Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ መንግስት ሰራተኞች ከተመረጡ የሥራ ሂደት ክፍል ውጪ ያሉ ሰራተኞች ላልተወሰነ ጊዜ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ ከተመረጡ የሥራ ሂደት ክፍል ውጪ ያሉ ሰራተኞች ላልተወሰነ ጊዜ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ተወሰነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንዳስታወቁት፥ “መንግስት ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ ወሳኝ የሥራ ሂደት ሰራተኞ ከሆኑት ውጪ ላልተወሰነ ጊዜ ከቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ተወስኗል” ብለዋል።

ውሳኔው የመብራት አገልግሎት፣የውሀ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት ዘርፍ፣መንገዶችና ኮንስትራክሽን እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻ ማንሳት ዘርፍ ላይ ያሉ ሰራተኞችን እንደማያካትት ተገልጿል።

በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎችና የፖሊስ አባላት የተለመደው ስራቸውን በተጠናከረ መልኩ እንደሚያከናውኑ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.