Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በኮሮናቫይረስ ዙሪያ ከሙሳ ፋኪ ማህማት፣ ከቶኒ ብሌርና ጎርደን ብራውን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮሮናቫይረስን (ኮቪድ 19) መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች  ዙሪያ ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መሪዎች ጋር መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  በጉዳዩ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት እንዲሁም ከቀድሞ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቶኒ ብሌር እና ጎርደን ብራውን ጋር ነው የተወያዩት።

በውይይታቸውም የአፍሪካ መሪዎች በጋራ በመሆን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) ፈታኝ ሁኔታ በአህጉር ደረጃ እንዴት ለመወጣት እንደሚቻል መምካራቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ ያመለከቱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.