ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአኮ ከተማ ያስገነባውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መረቁ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን አኮ ከተማ ያስገነባውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርቀው ከፍተዋል።
ትምህርት ቤቱ የተገነባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመደመር መጽሃፍ ሽያጭ ያገኙትን ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ እንዲሆን ለቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ባደረጉት ድጋፍ አማካኝነት ነው።
ለምረቃ የበቃው ትምህርት ቤት 18 መማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ የላይበራሪና የላቦራቶሪ ማዕከላትን የያዘ ነው።
በአልዓዛር ታደለ