የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015፣ ( ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።
ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን፥ ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ ለመካፈል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።
በአልዓዛር ታደለ