Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው  

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30 2015 (ኤፍ ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው፡፡

 በውይይቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደገለፁት÷በአገራዊ ምክክር ሒደት ውስጥ ሁሉም ክልልና ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሳተፉ ለማድረግ የተጠናከረ ተግባር እየተከናወነ ነው።

 ኮሚሽኑ ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

 ኢትዮጵያ የትኛውንም ተቃርኖና አለመግባባት ለመፍታት በርካታ እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ፕሮፌሰር መስፍን÷ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

 ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለህዝብ ቅርብ የሆኑ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

 ዛሬ ከሶስቱ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር የሚደረገው የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ የዚሁ አላማ አንዱ አካል ነው ብለዋል።

 ተወካዮቹ ስለ አገራዊ ምክክር አስፈላጊነትና ሂደት የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ በማንቃትና በማስገንዘብ ረገድ በሀላፊነት መስራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

 ኮሚሽኑ ወደ ህዝቡ ወርዶ ከማወያየቱ በፊት ዛሬ የሚገኘው የሀሳብ ግብዓት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.