የፋሲል ከነማና ሴፋክሲያን ጨዋታ 0 ለ 0 ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማና ሴፋክሲያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ያደረጉት የማጣሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 ተጠናቋል፡፡
አጼዎቹ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከቱኒዚያው ሴፋክሲያን ጋር ዛሬ አድርገዋል።
ጨዋታውን በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አፄዎቹ የሜዳቸውን እድል መጠቀም አልቻሉም።
ፋሲል ከነማና ሴፋክሲያን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታቸውን ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በቱኒዚያ እንደሚያደርጉ ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ክለብ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙር (ሦስተኛ ዙር) የሚያልፍ ይሆናል።