ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣዩ ሳምንት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተኛ የሚወስዱ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው፡፡
የወጣው መርሐ ግብር እንደሚያመላክተው÷ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ይጀምራል፡፡
የዘንድሮው 12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑን ተከትሎ ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል፡፡
በዚህም መሰረት÷ ወሎ፣ ጎንደር፣ ሠመራ፣ ደብረማርቆስ፣ ጅማ፣ ዲላ፣ ወልዲያ፣ባሕርዳር፣ ድሬዳዋ፣ ሐረማያ፣ ደብረ ታቦር፣ ቦንጋ፣ ጅግጅጋ፣ ደምቢ ዶሎ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መቀበል ጀምረዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ቅበላ በቀጣዮቹ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!