Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፊታችን መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡
 
የትምህርት ሚኒስቴር በፈተና ማዕከላት (ዩኒቨርሲቲዎች) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ ለፈታኞች የተከለከሉ ነገሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
 
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮችም የሚከተሉት ናቸው ፡-
 
• ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ፣
 
• ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስቲኮች ይዞ መገኘት፣
 
• ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ ፣ ፎቶ የሚያነሳ ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይፓድ፣ ታብሌት ኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውንም ፎቶ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም፣
 
• በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም ፣
 
• ማንኛውም አደንዛዥ እጸች (ጫት፣ ሲጋራ፣ የሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም ፣
 
• ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም ፣
 
• ማንኛውም አይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፣ ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)፣
 
• ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት፣
• ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት፣
 
• በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም ፣
 
• በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.