Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከሐምሌ እስከ መስከረም አጋማሽ 163 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 2015 ዓ አጋማሽ ድረስ ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸው ተገለጸ።

ከመስከረም 15 በኋላ የሚከስተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ያለመ ውይይት የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።

የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ፥ የወባ ወረርሽኝ ተጋላጭ በሆኑ ወረዳዎችና ዞኖች በልዩ ሁኔታ የመከላከል ስራ ካልሰራን ችግሩ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት ብቻ 3 ሺህ በወባ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት መደረጉንም ነው የገለጹት።

በጤና ኬላዎች የወባ ህክምና በተገቢው መንገድ እንዲሰጥ ሊደረግ ይገባልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ፥ የወባ በሽታ ስርጭቱ ከፍ ብሏል ነው ያሉት።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች በትኩረት ከሰራን በወባ ምክንያት ሞት እንዳይከሰት ማድረግ እንችላለንና ሁላችንም ከወዲሁ በትኩረት ልንስራ ይገባል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ በክልሉ የሚገኙ የሁሉም ዞኖች የጤና መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሰላም አስመላሽ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.