Fana: At a Speed of Life!

የደመራና የመስቀል  በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በመላው ሀገሪቱ የተከበረው የደመራና የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል አስታወቀ፡፡

የጋራ ግብረኃይሉ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ተጋላጭ ቦታዎችንና አካባቢዎችን ለይቶ÷ በቅድመ መከላከል ሥራ ላይ በርካታ የሰው ኃይል አሰማርቶ ከሕዝቡ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶችና ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ  በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ሕዝብባ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ለወጣቶች ግብረ ኃይሉ  አመስግኗል፡፡

የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎችም ከህብረተሰቡና ከበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ስለተወጡ ግብረኃይሉ  ምስጋና አቅርቧል፡፡

የሀገሪቱ ጠላቶችና አሸባሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በደኅንነት ላይ አደጋ ለማድረስ ስለሚጥሩ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ እያሳየ ያለውን ቀና ትብብር ወደፊት በሚከበሩ ሌሎች ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረኃይሉ  ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.