ከንቲባ አዳነች የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በማድረግ ሕዝቡን አመሰገኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ተቀናጅተው በመስራት ላሳዩት የላቀ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ላስገኙት ውጤት ምስጋና አቀረቡ።
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን፣ ትውፊቱንና እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷ የመላው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ፣ የእምነት አባቶች ፣ ምእመናን ፣ ወጣቶች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ ኃይሎች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እና ደንብ ማስከበር አገልግሎት ሌት ተቀን ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅተው እና ተሳስረው በመስራት ላሳዩት የላቀ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ላስገኙት ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
“አንድነታችን እና ህብረታችን መድመቂያ ጌጣችን ፣ በዓሎቻችን የአብሮነታችን መገለጫ፤ የኢትዮጵያዊነታችን ምሥጢር ናቸው ” ሲሉ ከንቲባ አዳነች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡