አቶ ደመቀ መኮንን ከሩስያና ማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጉባዔው ጎን ለጎን ከሩስያ እና ማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።
አቶ ደመቀ ከሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በውይይታቸው ላይ ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉ ወቅት የተደረሱ መግባባቶች ያሉበት ደረጃ ላይ ተነጋግረዋል።
የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዶሌይ ዲኦፕ ጋርም ተወያይተዋል።
በውይይታቸው የአፍሪካን ህብረት በማጠናከር የአህጉሪቱን ጥቅም ማስጠበቅ እንደሚገባ መክረዋል።