የ6 አመት ህፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሰር ዋለ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6 አመት ህፃን በማገት 200 ሺህ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የሸኔ አባል እንደሆነ የተጠረጠረው ግለሰቡ የ6 አመት ህፃን በማገት 200 ሺህ ብር ከህጻኑ ወላጆች በመቀበል ልጁን ሆለታ ከተማ ጫካ ውስጥ ጥሎ መሄዱ ተገልጿል፡፡
ከዛም ዘነበ ወርቅ መናኸሪያ በመሳፈር ወደ ጅማ ከተማ ሊያመልጥ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ጅማ በር ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብሬ መሰል ወንጀሎችን ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የሚፈፅሙ ፀጉረ ልውጦች በመኖራቸው ማህበረሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኮልፌ ቀራኒዎ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡