Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዮርዳኖስ አማን ከተማ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ወደ ዮርዳኖስ አማን ከተማ ዛሬ በረራ ጀመረ።
 
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
አየር መንገዱ በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርገውን የበረራ አገልግሎት በማሳደግና የሁለቱን አገራት ሕዝቦች በማቀራረብ ረገድ በረራው ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አቶ መስፍን ተናግረዋል።
 
አየር መንገዱ የበረራ አገልግሎትን ለማሳደግ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ወደ ገበያው በማስገባት የበረራ ተደራሽነቱን እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።
 
በባንግላዴሽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም አየር መንገዱ ወደ አማን በሳምንት ሶስት ጊዜ የበረራ አገልግሎት ለማድረግ መጀመሩን አስደሳች ዜና ነው ብለዋል።
 
መስመሩ ለአየር መንገዱ 129ኛው ዓለም አቀፍ መዳረሻ ሲሆን÷ አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ በሳምንት 3 ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.