ፌስቡክ ለአነስተኛ የንግድ ስራወች የ100 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስ ቡክ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የንግድ ስራወችን ለማገዝ የ100 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።
ድጋፉ ዓለም ላይ ከ30 በላይ በሆኑ ሃገራት የሚገኙ 30 ሺህ አነስተኛ የንግድ ስራወችን ለማገዝ የሚውል መሆኑንም አስታውቋል።
ከገንዘብ ድጋፉ ባለፈም የማስታወቂያ ስራ በነጻ እንደሚሰራላቸውም ገልጿል።
ተቋማቱም የድጋፉ ተጠቃሚ ለመሆን ለኩባንያው ማመልከቻቸውን ከቀጣዮቹ ሳምንታት ጀምሮ ያስገባሉም ነው የተባለው።
የሚደረገው ድጋፍ እንደ ኪራይ፣ የሰራተኛ ወጪ፣ ከደንበኞች ጋር በተገናኘ ለሚሰጡት አገልግሎትና ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላሉም ብሏል ኩባንያው።
ስልጠና እና የተለያዩ ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደሚያደርግም ኩባንያው ገልጿል።
ዓለም ላይ ከ183 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተይዘዋል።
ምንጭ፦ foxnews.com
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision