የተለያዩ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ለጥምር ጦሩ ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች “ደማችን ለመከላከያችን”ለጥምር ጦሩ አባላት ደም ለግሰዋል፡፡
ዛሬ የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች እና ሠራተኞች በኢትዮጵያ የደምና ቲሹ ባንክ ደም መለገሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በደም ልገሳ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ እየተፋለመ ለሚገኘው ጥምር ጦር በሁሉም ዘርፍ አጋርነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
በተመሳሳይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ለጥምር ጦሩ ደም ለግሰዋል፡፡
ከደም ልገሳ በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተቋሙ ሠራተኞች መናገራቸውን የአግልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡