አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በፈጸመው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት አምስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት አለፈ፡፡
ከአምስቱ ሰዎች በተጨማሪ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ በርካታ ቤቶችም ወድመዋል ተብሏል፡፡
የአብርገሌ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ አዳነ እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ በአበርገሌ ወረዳ በልታርፍ እና ፍርጣጣ መንደሮች ንፁሃንን ያነጣጠረ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡
በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በልታርፍ መንደር አምስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ንጹሃን ሕይወት ሲያልፍ በአንድ ነዋሪ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን በብልጽግና ፓርቲ የዋግኽምራ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡