የተቋማትን እቅድና አፈጻጸም የሚለካ ዘመናዊ ስርዓት በቴክኖሎጂ መታገዙ ውጤት አምጥቷል ተባለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተቋማትን እቅድና አፈጻጸም በዲጂታል መንገድ በመከታተል የሚለካ ዘመናዊ ስርዓትን በመዘርጋት ክትትልና ግምገማው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ፡፡
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ ከዘርፉ አመራሮችና አማካሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የታቀዱ የተቋማት እቅዶች በተቀመጠላቸው ጊዜና ግብ መሰረት መፈጸማቸውን መከታተልና መገምገም መደገፍና መከታተል ከዘርፋ ይጠበቃል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
አሁን የተተገበረው አዲሱ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አደረጃጀት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
የተቋማትን እቅድና አፈጻጸም በዲጂታል መንገድ በመከታተል የሚለካ ዘመናዊ ስርዓትን ወይም የዲጂታል ክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት ክትትልና ግምገማው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ስራ አስፈጻሚዎችና አማካሪዎችም ሀገራዊ የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ የክትትልና ግምገማ ስራን በተጠናከረ መንገድ ለማከናወን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሀገራዊ የክትትልና ግምገማ ዘርፍ የተቋማትን እቅድና አፈጻጸም በሪፖርት ፣ በጋራ መድረክና ጉብኝት በማድረግ ለሀገራዊ እቅድ ተፈጻሚነት ይሰራል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!