Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ለ59 ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ59 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡

የክልሉ መንግስት ይቅርታ ያደረገው የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ 59 ታራሚዎች መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ዜጎችም ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ከተለያዩ ወንጀሎች ራሳቸውን ጠብቀው በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.