አሸባሪው የከፈተውን ጦርነት እየተከላከልን የብልጽግና ጉዞ እናስቀጥላለን – አቶ መለሰ ዓለሙ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ እጃችን አሸባሪው ህወሓት የከፈተብንን ጦርነት እየተከላከልን በሌላኛው የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ እናስቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ገለጹ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ60/90 ቀናት ከተሰሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውና ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተገነቡት 70 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመርቀዋል፡፡
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት አቶ መለሰ ዓለሙ ፥ ፕሮጀክቶቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በ60 ቀናት የተጓተቱትን በማጠናቀቅ እና አዲስ ፕሮጀክቶችን በመጀመር በአጭር ጊዜ ውስጥ በወጪ ቆጣቢነት በጥራት ከተጠናቀቁት ፕሮጀክቶች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል።
የበጎ ፈቃደኝነት አሻራ ከሆነው ፕሮጀክት በጎነትን፣ መተሳሰብንና መረዳዳትን የሚያጠናክር መሆኑንም አስረድተዋል።
በዚህ ዓመት ብቻ 40 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 8 ሺህ መሰል ቤቶች እየተሰሩ ለተጠቃሚዎች እየተላለፉ እንደሚገኙ ገልጸው ፥ የህብረተሰቡንና የባለሀብቱን የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር አድንቀዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ ፥ ዛሬ የተመረቁት ቤቶች አረንጓዴ ልማትን፣ ቤተመፅሐፍት፣ 24 መታጠቢያ ቤቶች፣ 36 መፀዳጃ ቤቶችና ሰባት ሱቆችን የያዘ መሆኑን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በጋራ መኖሪያ ቤት ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ያስሚን ዋሀቢረቢ እና ሌሎችም የከተማና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ክፍለ ከተማው በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈፀማቸው ፕሮጀክቶች ጉልህ ሚና የነበራቸውን ተቋማትና ግለሰቦች ተመስግነዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!