Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ለሽብር ወንጀል ማስፈጸሚያነት ሊውሉ የነበሩ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ለጥፋት ኃይሎች የሽብር ወንጀል ማስፈጸሚያነት ሊውሉ የነበሩ 55 ሕገ ወጥ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች መያዛቸውን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡነክ ኡቦኖ እንደገለጹት÷ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎቹ የተያዙት ትናንት ምሽት ከሌሊቱ 7ሰዓት አካባቢ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ፖሊስና ልዩ ሀይል ባደረገው ክትትል ነው።

በዚህም በዋትጋችና ፑልኮድ ቀበሌ መካከል 19 ባለሰደፍና 39 ታጣፊ በድምሩ 55 የክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለጥፋት ኃይሎች የሽብር ወንጀል ማስፈጸሚያነት ሊውሉ እንደነበር ኢንስፔክተር ኡነክ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ኃይሉ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለመግታት በሚያደረገው ጥረት ህብረተሰቡ የጀመረውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኢንስፔክተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.