Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገለፀ፡፡

ካቢኔው በዛሬው መደበኛ ስብሰባው ተወያይቶ ውሳኔ ካሳረፈባቸው አጀንዳዎች መካከል የከተማ አስተዳደሮችን መዋቅር ለማሻሻል የቀረበ አስተያየት ይገኝበታል።

በዚህም ካቢኔው በቀረበው ማሻሻያ ላይ ተወያይቶና ተገቢ የማሻሻያ ሃሳቦችን ጨምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ካቢኔው በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ከተሞች መስፋፋታቸው አይቀርም በሚል እሳቤ በአቅራቢያ አካባቢዎች ባሉ ቀበሌዎች እያደር እየተስፋፋ የመጣውን የመሬት ወረራ እንዴት መከላከልና አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም የመፍትሄ ሀሳቦችንና የአፈፃጸም አቅጣጫዎችን ማቀመጡን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ-መስተዳድርና ካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.