Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የደረሰ የመኪና አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ  ልደታ ክፍለ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ትናንት ምሽት 2፡30 አካባቢ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አብነት አካባቢ ነው የደረሰው።

አደጋውን ያደረሰው ከሰባተኛ ወደ ዳርማር አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ መኪና መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በአደጋው የ38 ዓመት ጎልማሳ የቤት አውቶሞቢል አሽከርካሪ ሕይወቱ ሲያልፍ እስካሁን ባለው መረጃ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና ሰባት መኪናዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን አስታውቀዋል፡፡

የአደጋው መንስዔም በመጣራት ላይ መሆኑንን ኮማንደር ማርቆስ ገልፀዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.