የገቢዎች ሚኒስቴር በየካቲት ወር 19 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የገቢዎች ሚኒስቴር በየካቲት ወር 2012 19 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ገቢው የሀገር በቀል ኢኮኖሚን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሰብሰቡን ነው ያስታወቀው።
ሚኒስቴሩ በየካቲት ወር ር 20 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 19 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 95 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡
በዓመቱ መጀመሪያ 248 ቢሊየን ብር ለመሰብስብ አቅዶ የነበረ መሆኑን ገልጾ÷ነገር ግን በቅርቡ ለሀገር በቀል ተጨማሪ ኢኮኖሚ 20 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ኃላፊነት መውሰዱን አስታውቋል።
በዚህም ሚኒስቴሩ በዓመቱ መጨረሻ 270 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ እቅድ በፊት በየካቲት ወር 18 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ለመቀሰብሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን የእቅዱን በመቶ በመቶ ማሳካቱን ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በዚህ ወር ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ገቢ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረሃ ያመለክታል።