በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ።
የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ከምድብ 1 አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ13:24.44 በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆኖ በመግባት ቀጥታ ሲያልፍ አትሌት በ13:24.77 በሆነ ሰዓት 7ኛ የገባው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ማጣሪያውን አላለፈም።
ከምድብ 2 አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ 4ኛ በ13:14.87 ቀጥታ፤ አትሌት ሙክታር ኢድሪስ 7ኛ በ13:21.19 በተሻለ ሰአት አልፏል።
በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ድርቤ ኦልተጂ 1ኛ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ 2ኛ፣ ሃብታም አለሙ 1ኛ በመሆን ከየምድባቸው ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
በወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበረው አትሌት ቶለሳ ቦደና ከምድቡ 8ኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል።