በጋምቤላ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ መነሳቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡
በጋምቤላ ከተማ የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት 30 ድረስ ከሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አንስቶ መገደቡ እና ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!