Fana: At a Speed of Life!

የህንድ ቴሌኮም ኩባንያዎች  ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚያስችል  ዘመቻ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የህንድ ቴሌኮም ኩባንያዎች ሰዎች ስለ የኮሮናቫ ቫይረስ ያላቸውን ግንዛቤ ለመጨመር  የስልክ መጥሪያዎችን የማሳል  ድምጽ የማድረግ ዘመቻ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ዘመቻው በሀገሪቱ በመንግስት እየተሰራ ሲሆን የበሽታው ስርጭት በዜጎች መካከል የፈጠረውን ስጋት ለመግታት እና እራሳቸውን ከበሽታው እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ  ግንዛቤ  ለማስጨበጥ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

አርቲኤል ፣  ጂዮ ፣ ቢ.ኤስ.ኤን.ኤል ፣ ኤም.ቲ.ኤን.ኤል. ፣ ቮዳፎን  እና ታታ ዶኮሞ የተባሉት የህንድ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች  ዘመቻውን የተቀላቀሉ  ሲሆን፥ ሰዎችን ስለበሽታው ለማስታወስና ለማንቃት  ጥሪዎችን ሁሉ  በማሳል ድምጽ ማድረጋቸው ተነግሯል፡

ይህ የማሳል ድምጽ አንድ ሰው በኮረና ቫረስ ሲጠቃ የሚታይበት የመጀመሪያው ምልክት መሆኑን  ለማስታወስ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚያም ባለፈ መወሰድ ስለሚገባቸው የመከላከያ እርምጃዎች እንደሚያብራራም ነው የተነገረው፡፡

ዜማው  በእንግሊዝኛ ፣ በሂንዱ እና በሌሎች ቋንቋዎች  እንደሚገኝ ነው የተመላከተው፡፡

ምንጭ፡-ኢንድያ ቱዴይ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.