የሰላም ውይይት ሳይዘገይ መተግበር ለመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ እርቅ እና ብልጽግናን ያሳካል- የጀርመን መንግስት
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታ የሰላም ውይይት አስፈላጊ መሆኑን አንስቷል፡፡
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመቋጨት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እየተተገበሩ ያሉ አዳዲስ እርምጃዎች ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እንደሚወስዱም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
የሰላም ውይይት ሳይዘገይ መተግበሩም ለትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን፣ እርቅን እና ብልጽግናን እንደሚያሳክም አመላክቷል።