የጃፓኑ ካዋሳኪ ኢንዱስትሪ አረጋውያንን ያግዛል ያለውን ባለ አራት እግር ሮቦት አስተዋወቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ ካዋሳኪ ኢንዱስትሪ በእድሜ የገፉ የማህበረሰብ ክፍሎች ይጠቀሙበታል ያለውን ባለ አራት እግር ሮቦት ሰርቷል፡፡
“ቤክስ” የሚል መጠሪያ ያለው ሮቦት በአራት እግሩ መንቀሳቀስ የሚችል ሲሆን ጠፍጣፋና ጠፍጣፋ ወለል በሌለው የመሬት ክፍል ላይ በፍጥነት መጓዝ ይችላል ነው የተባለው፡፡
ሮቦቱ እርጅና የተጫናቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከቦታ ቦታ ሲጓጓዙ ለማገዝ ይረዳል ነው የተባለው።
በግብርና፣ በደን ልማት እና በኢንዱስትሪ ስራዎች ሰዎች ከባባድ ጭነቶቸን ሊያጓጉዙበት ይችላሉ ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ