የኢትዮጵያ ቡና በቀጥታ ወደ አልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና በቀጥታ ወደ በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ ምክክር ተካሄደ፡፡
በአልጀሪያ ልዩ ጣዕም ቡና ቆልቶ ለገበያ በማቅረብ ከሚታወቀው ፌኔክ ኮፊ ኩባንያ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያን ልዩ ጣዕም ቡና ወደ አልጄሪያ ገበያ ለማቅረብ ውይይት ተካሂዷል።
በአልጀርስ የኢፌድሪ ኤምባሲ ከኩባንያው ኃላፊዎቸ ጋር በተደረገው ውይይት ከኢትዮጵያ ላኪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መጀመሩ የዋጋና የጥራት ተጠቃሚ እንደሚያደርገው ቢታወቅም÷ በተለያዩ ምክንያቶች ገበያው በሦስተኛ ወገን በኩል ሲካሄድ መቆየቱን ኃላፊዎች አስታውቀዋል።
ኤምባሲው ላኪና ተቀባይን የማገናኘት ሚናውን እንደሚወጣ ለኩባንያው ኃላፊዎች መገለጹን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አልጀሪያ በአፍሪካ በነፍስ ወከፍ ቡና ተጠቃሚነት በአንደኛ ደረጃ ትገኛለች።