የቻይናው የበይነ መረብ ደህንነት ኩባንያ ሲ አይ ኤ ለ 11 ዓመታት ብርበራ ፈጽሟል ሲል ከሰሰ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የበይነ መረብ ደህንነት ኩባንያ የአሜሪካው የስለላ ተቋም (ሲ አይ ኤ) ለ11 ዓመታት ብርበራ ፈጽሟል ሲል ከሶታል።
ቂሆ 360 የተሰኘው ፀረ ቫይረስ አምራች ኩባንያ ሲ አይ ኤ የቻይናን የአየር ትራንስፖርት፣ የሃይል፣ የሳይንስ ምርምር ተቋማት፣ ኢንተርኔት አቅራቢዎች እና የመንግስት ተቋማትን ኢላማ ያደረጉ ብርበራዎች መፈጸሙን አስታውቋል።
ብርበራው አስፈላጊና ወሳኝ የጉዞ መስመሮችን ለመከታተልና ለመለየት ያለመ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።
የአሁኑ ውንጀላ ዊኪሊክስ በፈረንጆቹ 2017 ሲ አይ ኤ ፈጽሟቸዋል ብሎ ካወጣቸው የመረጃ መረብ ብርበራዎች አንደኛው ነው።
ይህም ከበይነ መረብ ብርበራ ጋር ተያይዞ በሲ ኤይ ኤ እና አሜሪካ ላይ የቀረበ ትልቁ ውንጀላ ነው ተብሏል።
ከቀረበው ውንጀላ ጋር ተያይዞ ግን እስካሁን ሲ አይ ኤም ሆነ አሜሪካ ያሉት ነገር የለም።
ምንጭ፦ ሬውተርስ