የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ በሀዋሳ በመከበር ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምባላላ በዓል በደመቀ መልኩ በሀዋሳ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል ።
ፊቼ ጨምባላላ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀምሯል። በትናንትናው እለት የበዓሉ አካል የነበሩ የተለያዩ ሁነቶች ተከናውነዋል።
በዛሬው እለትም ሰፊ ህዝብ የሚሳተፍበት የጫንባላላ በዓል እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን፥ በዓሉ በጉዱማሌ ሰፊ ህዝብ በተገኘበት በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ እየተካሄደ ነው።
ጨምባላላ ልጅ አዋቂው የሚደሰትበት ባህላዊ ክዋኔዎች በስፋት የሚታይበት ልዩ አውድም ነው።
ዛሬም ከንጋት ጀምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ የባህሉ ባለቤቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው በቄጣላ ክዋኔና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች አጅበው በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።
በበዓሉ ላይም የፌደራልና የክልሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታዳሚ ይሆናሉ።
በብርሃኑ በጋሻው