Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን በርካታ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች በመንከባከብ ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል- መሀመድ አል አሩሲ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ሀገር በመሆኗ በውስጧ የሚገኙ በርካታ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አቶ መሀመድ አል አሩሲ ተናገሩ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተሟቹና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት መሀመድ አል አሩሲ በሀረሪ ክልል የሚገኙ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ጎብኝተዋል፡፡
ሀረር ከተማ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሰላም፣ በፍቅር፣ በመቻቻልና በአብሮነት መኖሪያ መሆኗን አይቻለሁ፤ በመሆኑም ከተማዋ ይህን እሴቷን ጠብቃ እንድትቀጥል ሁሉም በጋራና በአንድነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ከተማዋ የብዙ ሺህ ዓመት ታሪክ ያላት መሆኗን መገንዘባቸውን ጠቁመው÷ የክልሉን ታሪክ፣ ቅርስና እሴቶች ለሌላው ዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
የክልሉ መገለጫ የሆኑ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ሁሉም ማህበረሰብ ሊንከባከባቸውና ሊጠብቃቸው እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ሀገር መሆኗን ያነሱት አቶ መሃመድ÷ በውስጧ የሚገኙ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
ትውልዱ ባህሉንና እሴቱን ጠንቅቆ ከመረዳትና ከመጠበቅ ባለፈም ለሌላው ማህበረሰብ ሊያሳውቅ ይገባል ማታቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.