ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የኢፍጣር ዝግጅት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማምሻውን ለተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የኢፍጣር ዝግጅት አድርገዋል።
በቤተ መንግስት በተካሄደው በኢፍጣር ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ፥ ሌሎች የእስልምና እምነት አባቶች እና የተለያዩ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ”ከዒድ እስከ ዒድ ወደ አገር ቤት ” በሚል መርህ በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፥ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እንግዶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝርዝር መርሐ ግብር ወጥቶ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!