Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአራት ሀገራት ለታዳሽ ሀይል ማስፋፊያ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ድጋፉን ያጸደቀው በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በጂቡቲ እና በሱዳን በረሃማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኙ ነው።

ድጋፉ በሀገራቱ በረሃማ አካባቢዎች የታዳሽ ሀይል ለማምረት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የተደረገ መሆኑን ቦርዱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አሁን የተደረገው ድጋፍ የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ከሚደግፋቸው 15 ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን፥ ለሀገራቱ የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ እንዲሆን በፀሐይ ሀይል የሚመረት ሀይል ፓርክ ጥናትን፣ ሀገራቱን በሀይል የሚያስተሳስር የሀይል ቋት ግንባታን፣ ከፍተኛ ሀይል የሚሸከም ገመድ ዝርጋታን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።

ድጋፉ በቀጠናው የታዳሽ ሀይል ማበልጸግ ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት የሚሞላ ከመሆኑም በተጨማሪ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰትን ችግር ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.