በመዲናዋ ከሕገወጦች የተያዘው ከ750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ መከፋፈሉን ቢሮው ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ የቁጥጥር ስራ ከሕገወጦች የተያዘው ከ 750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ መከፋፈሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ።
ቢሮው የዘይት አቅርቦት ማነስና የዋጋ መጨመር ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝም አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ቢሯቸው በተለያዩ ጊዜያት ባደረገው የቁጥጥር ስራ ከሕገወጦች የያዘውን ከ750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ ማከፋፈል ችሏል።
ሕገወጥ ነጋዴዎቹ ዘይቱ የተወረሰባቸው ገበያው እየፈለገው በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ገበያ ባለማቅረባቸውና የዘይት ምርቱ አዲስ አበባ ከተማ ገበያ መቅረብ እያለበት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲጭኑ በመገኘታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮም ዘይቱን ከነጋዴዎቹ በመውሰድ ለሸማች ሕብረት ስራ ማሕበራት ማስረክቡን አመልክተው፤ ማሕበራቱ ዘይቱን ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ማከፋፈላቸውንም አቶ አደም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!