የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና የሰሜን ሸዋ ዞን አጎራባች አካባቢወች የሰላም የውይይት መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርና የሰሜን ሸዋ ዞኖች አጎራባች አካባቢወች የሰላም የውይይት መድረክ በከሚሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ አካባቢውን የሰላም ቀጠና ለማጠናከር የጋራ እና የቅንጅት ሥራ እንደሚያስፈልግ የተነሳ ሲሆን÷ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የአመራር ግንኙነቱን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የሁለቱም የዞን አመራሮች እያደረጉት ያለው የጋራ የሰላም የምክክር መድረክ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ምቹ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በአካባቢው አሁን ላይ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ለማደፍረስና አብሮነቱን ለማጠልሸት የሚጥሩ ቡድኖችን በጋራ መታገል እንደሚገባም ነው ተሳታፊዎቹ የገለጹት፡፡
ውይይቱን የመሩት የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከድር አሊ የአካባቢውን ሰላም ለማጠናከር ውይይቱ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ የሁለቱም ዞኖች የሥራ ኃላፊዎችና እና የፀጥታ አካላት ተሳትፈዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!