በአፋር ክልል በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ ለክልሉ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
ዛሬ በተካሄደው የምስጋና መርሐ ግብር ÷ በክልሉ በህልውና ዘመቻ ወቅት በብቃት እና በታታሪነት ለተሳተፉ ለክልሉ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች የእውቅና፣ የምስጋና እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ።
የምስጋና መርሐ ግብሩ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የጤና ሠራተኞች ሣምንት በሰመራ ከተማ በተከበረበት ወቅት ነው።
በዕለቱም የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!