አራት ኢትዮጵያዊ እንስት ዳኞች የዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አራት ኢትዮጵያዊ እንስት ዳኞች የዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያን ጨዋታን እንደሚመሩ ካፍ አስታወቀ፡፡
በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለመካፈል ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በማጣሪያው ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምትጫወት ሲሆን፥ ብሩንዲ እና ታንዛኒያ ደግሞ ቡጃምቡራ ላይ ቅዳሜ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ይህንን ጨዋታም 4 ሴት ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንደሚመሩት ካፍ አስታውቋል፡፡
ጨዋታውን ፀሀይነሽ አበበ በመሃል ዳኝነት ሲመሩት፥ ወይንሸት አበራ፣ ወጋየሁ ዘውዴ እና ምስጋና ጥላሁን ደግሞ ጨዋታውን በረዳት ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!