Fana: At a Speed of Life!

የሀሰተኛ ማስረጃዎች መበራከት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ፈተና ሆኗል- የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ መታወቂያ፣ የጋብቻ ምስክር ወረቀት እና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መምጣት ለአገልግሎት አሰጣጡ ፈተና ሆኖብኛ ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃ እየተባባሰ በመምጣቱ በስራቸው ላይ ጫና መፍጠሩን ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 231 ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃዎችን መያዛቸውን ገልጸው÷ 152ቱ ሀሰተኛ መታወቂያ 26 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ያላገባ ማስረጃ መሆኑን ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧ፡፡
ወንጀሉ አድማሱን እያሰፋ ሀሰተኛ የቦታ ካርታ ሁሉ እየተዘጋጀ በመሆኑ÷ ችግሩን ለመቅረፍ ክልሎችም ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ኢሳ ቦሩ በክፍያ ስርዓት ላይ ያለው የሰዎች መጉላላት መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ገልጸው÷ የሀሰተኛ ሰነድ ማስረጃዎችን ለመከላከል ከክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.