ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀሰተኛ ሰነድ ወደ መሀል ሀገር ሊያልፍ የነበረ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅ ዛሬ መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርንጫፍ የጪጩ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ።
የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሀላፊ ምክትል ኮማንደር መስቀሌ አርጋው ለኢዜአ እንዳሉት ፥ ልባሽ ጨርቁ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3 09117 ኢት በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ ከቡሌ ሆራ አዲስ አበባ በሚል በተጻፈ ሀሰተኛ የቡና ማጓጓዣ ሰነድ ሊያልፍ ሲል ተይዟል።
የኬላ ፍተሻ ባለሙያዎች ሰነዱን በመጠራጠር ባደረጉት ማጣራት ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱን አመልክተው ፥ በፍተሻው ከቡና ገለባ ስር የተጫነ 10 ሺህ 931 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅ መገኘቱን ተናግረዋል።
በኬላ ፍተሻ ሂደት አሽከርካሪው ለጊዜው በማምለጡ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል እየተደረገበት መሆኑንም አስታውቀዋል።
በፌዴራል ፖለሲ የመቆጣጠሪያ ጣቢያው የጸጥታ አካላት አስተባባሪ ዋና ሳጅን ሀምሳሉ ለማ ፥ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ በሀሰተኛ ሰነድ ኬላን ለማለፍ የሚደረግ ሙከራ እየተበራከተ መምጣቱን ጠቁመዋል።
የመረጃ ልውውጥን በማጠናከር ህገ ወጥ ሰነዶችን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!