Fana: At a Speed of Life!

ከመላው ዓለም በመሰባሰብ ዒድን በጋራ ለማክበር የቀረበው ጥሪ አንድነታችንን የምናሳይበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው -የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመላው ዓለም በመሰባሰብ ዒድን በጋራ ለማክበር የቀረበው ጥሪ አንድነትና ትብብራችንን በተግባር የምናሳይበት ልዩና ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከየትኛውም ዓለም ለዒድ በዓል የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ፥ ዒድን በኢትዮጵያ በታላቅ ሁኔታ ለማክበር በተደረገው ጥሪ ተደስተናል ብለዋል።
ከየትኛውም ዓለም መጥተው ዒድን አብረውን የሚያከብሩትን ሁሉ ልንቀበላቸው ተዘጋጅተናል ነው ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር፡፡
በድርቅና ጦርነት የተጎዱ ወገኖችን በመተጋገዝ ድጋፍ ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጠርና የተፈናቀሉና በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችም እንደሚደገፉ ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ የመስጂዶችና የአውቃፍ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሸህ መሀመድ ሃሚዲን በበኩላቸው፥ በዓሉን በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በመሰባሰብ ማክበራቸው ይበልጥ አንድነትና ወንድማማችነታቸውን የሚያሳዩበት ነው ብለዋል።
በመሆኑም ለበዓሉ ድምቀትና እንግዶችን ለመቀበል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ከዒድ እስከ ዒድ ወደ ሀገር ቤት” በሚል በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊሞች እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ተገኝተው በዓላትን እንዲያከብሩ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.