ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ መደበኛ ጉባኤው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የስምንት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።
ለምክር ቤቱ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ፥ ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 52 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በተጠቀሰው ወራት ከዘርፉ 2 ነጥብ 77 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው ከእቅዱ 91 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ከግብርናው 1 ነጥብ 75 ቢሊየን፣ ከኢንዱስትሪ ዘርፉ 320 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር፣ ከማዕድን ዘርፍ 389 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ተጨምረውበት በድምሩ 2 ነጥብ 52 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!