Fana: At a Speed of Life!

የሀገረመቆር – ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 በመንግስት በተመደበ 1 ቢሊየን 558 ሚሊየን 150 ሺህ ብር የተገነባው የሀገረመቆር – ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡

የመንገድ ፕሮጀከቱ 102 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ለትራፊክ ክፍት ሆኖ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ግንባታውን ያከናወነው ዓለም አቀፉ የሥራ ተቋራጭ “ቻይና ኮሙኒኬሽን የኮንስትራክሽን” ተቋራጭ ሲሆን፥ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ ስታዲያ ኢንጅነሪንግ ከጂ እና ዋይ ኢንጅነሪንግ በጥምረት አከናውነውታል።

የመንገዱ መገንባት በመስመሩ ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረውን ከፍተኛ የትራንስፖርት እንግልት በማስቀረት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አስችሏል ነው የተባለው።

መንገዱ በዋናነትም ጨረቲ ወረዳን ከጎሮ በቀቅሳ እና ከጎሮዳሞሌ ወረዳ ጋር የሚያስተሳስር ሲሆን፥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በገጠር 8 ሜትር፣ በቀበሌ 14 ሜትር እንዲሁም በወረዳ 19 ሜትር የጎን ስፋት ያለው መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መነሻውን ጨረቲ ከተማ ላይ አድርጎ ቁንዲ ከተማ ላይ የሚያበቃ ሲሆን የጨረቲ -ጎሮ በቀቅሳ- ጎሮዳሞሌ – ሀገረመቆር- ቁንዲ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አካል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

የዚህ መንገድ አካል የሆነው የጨረቲ- ሀገረመቆር ክፍል-1 መንገድ ግንባታው ቀደም ብሎ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.