በአማራ ክልል ለግማሽ ሚሊየን ያህል ሴቶች የማህፀን በር ጫፍ የካንሰር መከላከያ ክትባት ከመጋቢት 26 ጀምሮ ይሰጣል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱትን ጨምሮ ለግማሽ ሚሊየን ያህል ሴቶች የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ከመጋቢት 26 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ ፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ላይ በባህር ዳር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።
በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የክትባት ፕሮግራም አስተባባሪ ወርቅነህ ማሞ÷ እድሜያቸው 14 ዓመት የሞላ ሴቶች ክትባቱን እንደሚወስዱ ገልጸው÷ ከስድስት ወራት በፊት የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱ ሴቶች ሁለተኛውንና የመጨረሻውን ዙር ክትባት በአሁኑ ዙር እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርን ለመከላከል ከመጋቢት 26 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጠውን ክትባት ውጤታማ እንደሚያደርገው ተመላክቷል፡፡
ክትባቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ መሆኑን የጠቆሙት አስተባባሪው÷ ሁሉም ዜጋ ለክትባቱ ተፈጻሚነት ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!