Fana: At a Speed of Life!

1443 ኛው የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ ቅዳሜ መጋቢት 24  ይጀምራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለፀው፥  ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።

የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስማን አደም  ፆሙ ነገ እንደሚጀምር ተረጋግጧል ብለዋል።

ህዝበ ሙስሊሙም ፆሙን ሲያሳልፍ በተለመደው የመደጋገፍ የመረዳዳትና ባህል ሊሆን እንደሚገባ ምክር ቤቱ ገልጿል።

በተለይ በጦርነትና በድርቅ ከባድ ጉዳት ያስተናገዱ ብሎም የተፈናቀሉ ወገኖችን ማሰብ እጅጉን ሚያስፈልግበት ወቅት ነው ብለዋል።

በሂጅራ አቆጣጠር 9 ኛው ወር ረመዳን በመላው አለም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዬች በፃም እና ፀሎት የሚያሳልፉት ወር ነው።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.