Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ቁጥር 882/2014 ይፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክትባትን በሚመለከት ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ባለፉት 2 ዓመታት በኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠርና ለመግታት የተለያዩ መመሪያዎችንና ደንቦችን በማውጣት ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክትባትን ትኩረት የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ማዉጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው መመሪያ ቁጥር 882/2014 ይፋ የተደረገው፡፡
ተሻሽሎ በወጣው የኮቪድ-19 ወረርሽን መመሪያ 882/2014 መሰረት ከዚህ በፊት ሲተገበሩ ከነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎች የቀጠሉና ማሻሻያ የተደረገባቸው መኖራቸው ተመላክቷል።
በመመሪያ 803/2013 ተጥለው የነበሩና ከፊል ማሻሻያ የተደረገባቸው ክልከላዎች በመመሪያው መካተታቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
በአገራችን የክትባቱ አቅርቦት እና ስርጭት አበረታችና መንግስት በነፃ እየሰጠ በመሆኑ 25 ሚሊየን ዜጎች መከተባቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ÷ ይህም ቁጥር በሚደረገዉ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚጨምር ታሳቢ በማድረግ የነበሩትን የተወሰኑ ክልከላዎችና ግዴታዎች በማላላት ወይም በማስቀረት ይበልጥ ውጤታማ የሚሆን የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክትባትን ትኩረት የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መመሪያ ቁጥር 882/2014 ወጥቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.