የሰሜን ምስራቅ አካባቢ የኦፕቲካል ፋይበር መስመሮች ጥገና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞ የነበረውን የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች እና የኦፕቲካል ፋይበር ገመዶች የመጠገን ሥራ ተጠናቀቀ፡፡
ከደብረሲና – ሸዋሮቢት – ከሚሴ – ኮምቦልቻ – አቀስታ – ዓለም ከተማ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር፣ ከደብረ ብርሃን – ኮምቦልቻ – ሠመራ እና ከኮምቦልቻ – አላማጣ እስከ ቆቦ ድረስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ላይ ጥገና ተጠናቋል፡፡
በተመሳሳይ ከደሴ – ወልዲያ ባለ 66 ኪሎ ቪልት መስመር ጥገና ተጠናቆ የወልዲያ እና አካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡፡
በቀጣይ መስመሩ አገልግሎት እየሰጠ ችግሮች ቢገጥመው ችግሩን የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የጥገና ቢሮ እንዲፈታው እና እንደሚከሰተው ችግር ስፋት ደግሞ እገዛ በሚያስፈልገው ቦታ ላይ ከማዕከል የሚንቀሳቀስ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድን እገዛ እንዲያደርግ አቅጣጫ መቀመጡም ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!