Fana: At a Speed of Life!

የስልጤ ኤፍ ኤም 92 ነጥብ 6 የማህበረሠብ ሬድዮ ጣቢያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስልጤ ኤፍ ኤም 92 ነጥብ 6 የማህበረሠብ ሬድዮ ጣቢያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ።
የማህበረሰቡን የሚዲያ ፍላጎት በላቀ ደረጃ ያሟላል ተብሎ የታመነበት ይህ ጣቢያ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር በተገኙበት በይፋ የሙከራ ስርጭቱን ጀምሯል።
የኤፍ ኤም ጣቢያውን ተከላ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አከናውኖታል።
ለማህበረሠቡ የሬድዮ ጣቢያ መክፈት ለአመታት የቆየ የህዝብ ጥያቄ መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፥ የስልጤን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ይበልጥ እንደሚያስተዋውቅ ገልፀዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የህዝብ ድምፅ እና አንጋፋ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፥ አቶ አሊ ከድር፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአንቴና፣ የማሠራጫ መሣሪያ እና የስቱዲዮ ግንባታንና ተከላን ጥራት ባለው መንገድ ማከናወን በመቻሉም አመስግነዋል።
በሙከራ ስርጭት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሱርሞሎን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የስልጤ ህዝብ ማንነት የተረጋገጠበት ቀን ክብረ በዓል ካለፈው መጋቢት 20 ቀን 2014 ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ሲሆን፥ የዛሬውም ስነ ስርዓት የዚህ አካል ነው።
በተጫሪም በነገው እለት በስልጤ ህዝብ ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ምክትል ሀላፊ እና ዛሬ የሙከራ ስርጭቱን የጀመረው ኤፍ ኤም 92 ነጥብ 6 ስራ አስኪያጅ አቶ ሬድዋን ጀማል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በፓናሉ ላይም የአከባቢው ተወላጆች እና ከዞኑ የተውጣጡ የተለያዩ እንግዶች እንደሚካፈሉም ነው ያመለከቱት።
የዘንድሮው የስልጤ ህዝብ ማንነት የተረጋገጠበት 21ኛ ዓመት ሲሆን እየተከበረ ያለው፥ በዓሉ ሲከበር ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።
በሰላማዊት ተስፋዬ
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.