አሜሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ ከማዋል እንድትቆጠብ ቻይና ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በቻይና የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ላይ ያላትን የተሳሳተ አቀራረብ በአስቸኳይ እንድታርም የቻይና ንግድ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡
የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ÷ ቻይና በምታደርጋቸው የንግድ እንቅሥቃሴዎች ላይ ጫና በመፍጠር ኢኮኖሚዋን ለመጉዳት አሜሪካ ፖለቲካዊ ጫና እያሳደረች ነው ሲል ይከሳል፡፡
ሚኒስቴሩ አሜሪካ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና በመገናኛ ቁሳቁስ ሽያጭ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ “ቻይና ቴሌኮም አሜሪካስ” እና “ቻይና ሞባይል ኢንተርናሽናል ዩ ኤስ ኤ” የተሰኙትን የቻይና ኩባንያዎች ለብሔራዊ ደኅንነቴ ስጋት ናቸው ብላ መፈረጇን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሹ ጁቲንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ አሜሪካ ኩባንያዎቹን በዚህ መልኩ መፈረጇ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ ቻይና መብቷን ለማስከበርም አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ በቆራጥነት ትወስዳለች ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!